ኢዮብ 12:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የዘራፊዎች ድንኳን ሰላም አለው፤+አምላክን የሚያስቆጡ ሰዎችም፣አምላካቸውን* በእጃቸው እንደያዙ ሰዎች የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል።+ መዝሙር 12:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የሰው ልጆች ብልሹ ምግባርን ስለሚያስፋፉ፣ክፉዎች እንዳሻቸው ይፈነጫሉ።+ መክብብ 8:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በክፉ ሥራ ላይ በአፋጣኝ ፍርድ ስለማይሰጥ+ የሰው ልጆች ልብ ክፉ ነገር ለማድረግ ተደፋፈረ።+ ኢሳይያስ 1:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ታማኝ የነበረችው ከተማ+ እንዴት ዝሙት አዳሪ ሆነች!+ ፍትሕ የሞላባትና+ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤+አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ጎሬ ሆናለች።+ የሐዋርያት ሥራ 7:52, 53 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 52 ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ስደት ያላደረሱበት ማን አለ?+ አዎ፣ እነሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገድለዋቸዋል፤+ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ደግሞም ገደላችሁት፤+ 53 በመላእክት አማካኝነት የተላለፈውን ሕግ ተቀበላችሁ፤+ ነገር ግን አልጠበቃችሁትም።”
52 ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ስደት ያላደረሱበት ማን አለ?+ አዎ፣ እነሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገድለዋቸዋል፤+ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ደግሞም ገደላችሁት፤+ 53 በመላእክት አማካኝነት የተላለፈውን ሕግ ተቀበላችሁ፤+ ነገር ግን አልጠበቃችሁትም።”