13 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘“ስለ ሦስቱ የአሞናውያን ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም ግዛታቸውን ለማስፋት ሲሉ የጊልያድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀደዋል።+
14 በመሆኑም በራባ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤+
የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል፤
በውጊያው ቀን ቀረርቶ ይሰማል፤
አውሎ ነፋስ በሚነሳበትም ቀን ነውጥ ይኖራል።
15 ንጉሣቸውም ከመኳንንቱ ጋር በግዞት ይወሰዳል”+ ይላል ይሖዋ።’