ኤርምያስ 3:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ ሕዝቅኤል 37:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በትር ወስደህ ‘ለይሁዳና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ሰዎች’+ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ ‘ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትርና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ’+ ብለህ ጻፍበት። ሕዝቅኤል 37:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኤፍሬም እጅ ውስጥ ያለውን የዮሴፍንና ከእሱ ጋር ያሉትን የእስራኤልን ነገዶች በትር ወስጄ ከይሁዳ በትር ጋር አያይዘዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”’ ሆሴዕ 1:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “የእስራኤልም ሕዝብ* ብዛት ሊሰፈር ወይም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል።+ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’+ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ይባላሉ።+ 11 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ተሰብስበው አንድ ይሆናሉ፤+ ለራሳቸውም አንድ መሪ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።+
16 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በትር ወስደህ ‘ለይሁዳና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ሰዎች’+ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ ‘ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትርና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ’+ ብለህ ጻፍበት።
19 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኤፍሬም እጅ ውስጥ ያለውን የዮሴፍንና ከእሱ ጋር ያሉትን የእስራኤልን ነገዶች በትር ወስጄ ከይሁዳ በትር ጋር አያይዘዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”’
10 “የእስራኤልም ሕዝብ* ብዛት ሊሰፈር ወይም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል።+ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’+ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ይባላሉ።+ 11 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ተሰብስበው አንድ ይሆናሉ፤+ ለራሳቸውም አንድ መሪ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።+