-
ማርቆስ 1:29-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ ወጥተው ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት ሄዱ።+ 30 የስምዖን አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ ነበር፤ ስለ እሷም ወዲያው ለኢየሱስ ነገሩት። 31 እሱም ወደተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሳት። በዚህ ጊዜ ትኩሳቱ ለቀቃትና ታገለግላቸው ጀመር።
32 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ፣ ምሽት ላይ ሰዎች የታመሙትንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤+ 33 የከተማዋም ሰው ሁሉ በደጅ ተሰብስቦ ነበር። 34 ኢየሱስም በተለያየ በሽታ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ፈወሰ፤+ ብዙ አጋንንትንም አወጣ። ሆኖም አጋንንቱ ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ስለነበር* እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።
-
-
ሉቃስ 4:38-41አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት።+ 39 እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር።
40 ፀሐይ ስትጠልቅም ሰዎች በተለያየ በሽታ የተያዙ ሕመምተኞቻቸውን ወደ እሱ አመጡ። እሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።+ 41 አጋንንትም “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” እያሉና እየጮኹ+ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም አውቀው ስለነበር+ እንዳይናገሩ ከለከላቸው።+
-