ማቴዎስ 8:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት ሲመጣ የጴጥሮስ አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ አገኛት።+ 15 እጇንም ሲዳስሳት+ ትኩሳቱ ለቀቃት፤ ተነስታም ታገለግለው ጀመር። ሉቃስ 4:38, 39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት።+ 39 እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር።
38 ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት።+ 39 እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር።