የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማርቆስ 3:22-27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም “ብዔልዜቡል* አለበት፤ አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” ይሉ ነበር።+ 23 በመሆኑም ወደ እሱ ከጠራቸው በኋላ በምሳሌ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንዴት ሰይጣንን ሊያስወጣ ይችላል? 24 አንድ መንግሥት እርስ በርሱ ከተከፋፈለ ያ መንግሥት ጸንቶ ሊቆም አይችልም፤+ 25 አንድ ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ጸንቶ ሊቆም አይችልም። 26 በተመሳሳይም ሰይጣን በራሱ ላይ የሚነሳና የሚከፋፈል ከሆነ ያከትምለታል እንጂ ሊጸና አይችልም። 27 ደግሞም ወደ አንድ ብርቱ ሰው ቤት የገባ ሰው በቅድሚያ ብርቱውን ሰው ሳያስር ንብረቱን ሊሰርቅ አይችልም። ቤቱን መዝረፍ የሚችለው እንዲህ ካደረገ ብቻ ነው።

  • ሉቃስ 11:15-23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል* ነው” አሉ።+ 16 ሌሎች ደግሞ ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ይጠይቁት ጀመር።+ 17 ኢየሱስም ሐሳባቸውን አውቆ+ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ እንዲሁም እርስ በርሱ የሚከፋፈል ቤት ይወድቃል። 18 በተመሳሳይም ሰይጣን እርስ በርሱ ከተከፋፈለ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እናንተ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል እንደሆነ ትናገራላችሁና። 19 እኔ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ የሚያስወጧቸው ታዲያ በማን ነው? ልጆቻችሁ ፈራጆች የሚሆኑባችሁ ለዚህ ነው። 20 ሆኖም አጋንንትን የማስወጣው በአምላክ ጣት+ ከሆነ የአምላክ መንግሥት ሳታስቡት ደርሶባችኋል ማለት ነው።+ 21 አንድ ብርቱ ሰው በደንብ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ ንብረቱ ምንም አይነካበትም። 22 ይሁን እንጂ ከእሱ ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው ካጠቃውና ካሸነፈው ተማምኖበት የነበረውን መሣሪያ ሁሉ ይነጥቀዋል፤ ከእሱ የወሰደውንም ለሌሎች ያካፍላል። 23 ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ሁሉ ይበትናል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ