የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 6:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይሆናልና።

  • ማርቆስ 4:18, 19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በእሾህ መካከል እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑ ሌሎች ደግሞ አሉ። እነዚህ ቃሉን የሰሙ ናቸው፤+ 19 ይሁንና የዚህ ሥርዓት* ጭንቀትና+ ሀብት ያለው የማታለል ኃይል+ እንዲሁም የሌሎች ነገሮች ሁሉ ምኞት+ ወደ ልባቸው ሰርጎ በመግባት ቃሉን ያንቀዋል፤ የማያፈራም ይሆናል።

  • ማርቆስ 10:23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 ኢየሱስ ዙሪያውን ከተመለከተ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ አምላክ መንግሥት መግባት ምንኛ አስቸጋሪ ነው!” አላቸው።+

  • ሉቃስ 8:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 በእሾህ መካከል የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ሆኖም በዚህ ዓለም የኑሮ ጭንቀት፣ ሀብትና+ ሥጋዊ ደስታ+ ትኩረታቸው ተከፋፍሎ ሙሉ በሙሉ ይታነቃሉ፤ ለፍሬም አይበቁም።+

  • 1 ጢሞቴዎስ 6:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ሀብታም ለመሆን ቆርጠው የተነሱ ግን ፈተናና ወጥመድ+ ውስጥ ይወድቃሉ፤ እንዲሁም ሰዎችን ጥፋትና ብልሽት ውስጥ በሚዘፍቁ ከንቱና ጎጂ በሆኑ ብዙ ምኞቶች ይያዛሉ።+

  • 2 ጢሞቴዎስ 4:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ዴማስ+ በአሁኑ ጊዜ ያለውን ሥርዓት* ወዶ፣ ትቶኝ ወደ ተሰሎንቄ ሄዷልና፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶ ደግሞ ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ