ማቴዎስ 9:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ሕዝቡንም ባየ ጊዜ እረኛ እንደሌላቸው በጎች+ ተገፈውና ተጥለው ስለነበር እጅግ አዘነላቸው።+ ማቴዎስ 15:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ “እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ።+ እንዲሁ ጦማቸውን ልሰዳቸው አልፈልግም፤ መንገድ ላይ ዝለው ሊወድቁ ይችላሉ” አላቸው።+ ማርቆስ 1:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 በዚህ ጊዜ በጣም አዘነለትና እጁን ዘርግቶ ዳሰሰው፤ ከዚያም “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው።+ ማርቆስ 6:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ኢየሱስም ከጀልባዋ ሲወርድ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተመለከተ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች+ ስለነበሩም በጣም አዘነላቸው።+ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር።+ ሉቃስ 7:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ጌታ ባያት ጊዜ በጣም አዘነላትና+ “በቃ፣ አታልቅሺ”+ አላት። ዕብራውያን 2:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ*+ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ እንደ “ወንድሞቹ” መሆን አስፈለገው።+ ዕብራውያን 5:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እሱ ራሱ ድክመት ስላለበት* አላዋቂ የሆኑትንና የሚሳሳቱትን* በርኅራኄ* ሊይዛቸው ይችላል፤
32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ “እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ።+ እንዲሁ ጦማቸውን ልሰዳቸው አልፈልግም፤ መንገድ ላይ ዝለው ሊወድቁ ይችላሉ” አላቸው።+
17 ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ*+ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ እንደ “ወንድሞቹ” መሆን አስፈለገው።+