ኢሳይያስ 55:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+ ማቴዎስ 6:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የበደሉንን* ይቅር እንዳልን በደላችንን* ይቅር በለን።+ ማቴዎስ 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “እንግዲህ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው።+ ሕጉም ሆነ የነቢያት ቃል የሚሉት ይህንኑ ነው።+ ያዕቆብ 2:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ምሕረት የማያደርግ ሰው ያለምሕረት ይፈረድበታልና።+ ምሕረት በፍርድ ላይ ድል ይቀዳጃል።