ምሳሌ 21:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ችግረኛው የሚያሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን ሁሉ፣እሱ ራሱ ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።+ ማቴዎስ 5:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው፤+ ምሕረት ይደረግላቸዋልና። ማቴዎስ 6:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እናንተ ግን የበደሏችሁን ሰዎች ይቅር ካላላችሁ አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይላችሁም።+ ሉቃስ 6:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ።+