25 እነሆም አንድ ሕግ አዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነው ተነስቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው።+ 26 ኢየሱስም “በሕጉ ላይ የተጻፈው ምንድን ነው? አንተስ ምን ትረዳለህ?” አለው። 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። 28 ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው።+