ማቴዎስ 18:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ስለዚህ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው እንደዚህ ትንሽ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው፤+ ማቴዎስ 23:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይልቁንም ከመካከላችሁ ታላቅ የሆነው የእናንተ አገልጋይ መሆን ይገባዋል።+ ማርቆስ 10:43, 44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ 44 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ሊሆን ይገባል። ሉቃስ 22:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ።+ ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን፤+ አመራር የሚሰጥም እንደ አገልጋይ ይሁን።
43 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ 44 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ሊሆን ይገባል።