ሉቃስ 22:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ለመሆኑ በማዕድ ከተቀመጠና ቆሞ ከሚያገለግል ማን ይበልጣል? በማዕድ የተቀመጠው አይደለም? እኔ ግን በመካከላችሁ ያለሁት እንደ አገልጋይ ሆኜ ነው።+ ዮሐንስ 13:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ስለዚህ እኔ ጌታና መምህር ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብኩ+ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል።*+ ፊልጵስዩስ 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚህ ይልቅ ራሱን ባዶ በማድረግ የባሪያን መልክ ያዘ፤+ ደግሞም ሰው ሆነ።*+