ማቴዎስ 20:26, 27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤+ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ 27 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ባሪያችሁ ሊሆን ይገባል።+ ሉቃስ 9:48 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 48 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝንም ይቀበላል።+ ምክንያቱም ታላቅ የሚባለው ራሱን ከሁላችሁ እንደሚያንስ አድርጎ የሚቆጥር ነው።”+ ሉቃስ 22:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ።+ ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን፤+ አመራር የሚሰጥም እንደ አገልጋይ ይሁን። ሮም 12:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በወንድማማች ፍቅር እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ። አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ።*+ 1 ጴጥሮስ 5:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በተመሳሳይም እናንተ ወጣቶች፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ።+ ይሁንና እርስ በርስ ባላችሁ ግንኙነት ሁላችሁም ትሕትናን ልበሱ፤* ምክንያቱም አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።+
26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤+ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ 27 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ባሪያችሁ ሊሆን ይገባል።+
48 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝንም ይቀበላል።+ ምክንያቱም ታላቅ የሚባለው ራሱን ከሁላችሁ እንደሚያንስ አድርጎ የሚቆጥር ነው።”+
5 በተመሳሳይም እናንተ ወጣቶች፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ።+ ይሁንና እርስ በርስ ባላችሁ ግንኙነት ሁላችሁም ትሕትናን ልበሱ፤* ምክንያቱም አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።+