-
2 ዜና መዋዕል 24:20-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የአምላክ መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ+ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “እውነተኛው አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሖዋን ትእዛዛት የምትተላለፉት ለምንድን ነው? አይሳካላችሁም! ይሖዋን ስለተዋችሁ እሱም ይተዋችኋል።’”+ 21 እነሱ ግን በእሱ ላይ አሴሩ፤+ ንጉሡም በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።+ 22 ንጉሥ ኢዮዓስ፣ አባቱ* ዮዳሄ ያሳየውን ታማኝ ፍቅር አላሰበም፤ ልጁንም ገደለው፤ እሱም ሊሞት ሲል “ይሖዋ ይየው፤ የእጅህንም ይስጥህ” አለ።+
-