ማቴዎስ 26:57 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 57 ኢየሱስን ያሰሩት ሰዎች ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ወደተሰበሰቡበት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ+ ወሰዱት። ሉቃስ 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እንዲሁም ቀያፋና የካህናት አለቃው ሐና በነበሩበት ዘመን+ የአምላክ ቃል በምድረ በዳ+ ወደነበረው ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ+ መጣ። ዮሐንስ 11:49 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 ሆኖም ከመካከላቸው አንዱ፣ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ+ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ምንም አታውቁም፤ ዮሐንስ 18:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በመጀመሪያም ወደ ሐና ወሰዱት፤ ምክንያቱም ሐና በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት+ የነበረው የቀያፋ+ አማት ነበር። ዮሐንስ 18:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከዚያም ሐና ኢየሱስን እንደታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።+