ሉቃስ 18:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚያም ምንጊዜም ተስፋ ሳይቆርጡ የመጸለይን+ አስፈላጊነት በተመለከተ ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ ሮም 12:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በተስፋው ደስ ይበላችሁ። መከራን በጽናት ተቋቋሙ።+ ሳትታክቱ ጸልዩ።+ ኤፌሶን 6:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም ዓይነት ጸሎትና+ ምልጃ በማንኛውም ጊዜ በመንፈስ መጸለያችሁን ቀጥሉ።+ ለዚህም ሲባል ዘወትር ንቁ ሁኑ፤ እንዲሁም ስለ ቅዱሳን ሁሉ ምልጃ አቅርቡ። 1 ጴጥሮስ 4:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ሆኖም የሁሉም ነገር መጨረሻ ቀርቧል። ስለዚህ ጤናማ አስተሳሰብ ይኑራችሁ፤+ እንዲሁም በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ።+
18 ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም ዓይነት ጸሎትና+ ምልጃ በማንኛውም ጊዜ በመንፈስ መጸለያችሁን ቀጥሉ።+ ለዚህም ሲባል ዘወትር ንቁ ሁኑ፤ እንዲሁም ስለ ቅዱሳን ሁሉ ምልጃ አቅርቡ።