ማርቆስ 14:47 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 47 ይሁን እንጂ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት አንዱ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቆረጠው።+ ሉቃስ 22:50 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 50 እንዲያውም ከመካከላቸው አንዱ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው።+ ዮሐንስ 18:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚህ ጊዜ ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው።+ የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበር።