ማርቆስ 15:2-5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ጲላጦስም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው።+ እሱም መልሶ “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።+ 3 የካህናት አለቆቹ ግን በእሱ ላይ በርካታ ክስ መደርደራቸውን ቀጠሉ። 4 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “ምንም መልስ አትሰጥም?+ በስንት ነገር እየከሰሱህ እንዳሉ ተመልከት” ሲል እንደገና ጠየቀው።+ 5 ሆኖም ኢየሱስ ምንም ተጨማሪ መልስ አልሰጠም፤ በመሆኑም ጲላጦስ ተገረመ።+ ሉቃስ 23:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “አንተው ራስህ እኮ እየተናገርከው ነው” አለው።+ ዮሐንስ 18:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ስለሆነም ጲላጦስ ወደ ገዢው መኖሪያ ተመልሶ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” አለው።+ ዮሐንስ 18:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው።+ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው።+ ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።”
2 ጲላጦስም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው።+ እሱም መልሶ “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።+ 3 የካህናት አለቆቹ ግን በእሱ ላይ በርካታ ክስ መደርደራቸውን ቀጠሉ። 4 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “ምንም መልስ አትሰጥም?+ በስንት ነገር እየከሰሱህ እንዳሉ ተመልከት” ሲል እንደገና ጠየቀው።+ 5 ሆኖም ኢየሱስ ምንም ተጨማሪ መልስ አልሰጠም፤ በመሆኑም ጲላጦስ ተገረመ።+
37 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው።+ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው።+ ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።”