ዮሐንስ 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤+ በመካከላችንም ኖረ፤ አንድያ ልጅ+ ከአባቱ እንደሚያገኘው ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ እሱም መለኮታዊ ሞገስንና* እውነትን ተሞልቶ ነበር። ዮሐንስ 1:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ምክንያቱም ሕጉ የተሰጠው በሙሴ በኩል ነበር፤+ ጸጋና+ እውነት ግን የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው።+ ዮሐንስ 14:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እኔ መንገድ፣+ እውነትና+ ሕይወት+ ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።+