-
ሉቃስ 3:2-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 እንዲሁም ቀያፋና የካህናት አለቃው ሐና በነበሩበት ዘመን+ የአምላክ ቃል በምድረ በዳ+ ወደነበረው ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ+ መጣ።
3 ዮሐንስም ለኃጢአት ይቅርታ፣ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ሁሉ ሄደ፤+ 4 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ነው፦ “አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን* መንገድ አዘጋጁ! ጎዳናዎቹንም አቅኑ’ በማለት ይጮኻል።+ 5 ‘ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ ተራራውና ኮረብታው ሁሉ ይደልደል፤ ጠማማው መንገድ ቀጥ ያለ፣ ጎርበጥባጣውም መንገድ ለጥ ያለ ይሁን፤ 6 ሥጋም* ሁሉ የአምላክን ማዳን* ያያል።’”+
-