ማርቆስ 7:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 በዚያም* ሰዎች መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት+ አንድ ሰው ወደ እሱ አምጥተው እጁን እንዲጭንበት ተማጸኑት። 33 እሱም ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደው። ከዚያም ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።+ ዮሐንስ 9:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በመንገድ እያለፈ ሳለም ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነ አንድ ሰው አየ። ዮሐንስ 9:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይህን ካለ በኋላ መሬት ላይ እንትፍ በማለት በምራቁ ጭቃ ለወሰ፤ ጭቃውንም በሰውየው ዓይኖች ላይ ቀባ፤+
32 በዚያም* ሰዎች መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት+ አንድ ሰው ወደ እሱ አምጥተው እጁን እንዲጭንበት ተማጸኑት። 33 እሱም ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደው። ከዚያም ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።+