ማቴዎስ 10:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 ነፍሱን* ለማዳን የሚሞክር ሁሉ ያጣታል፤ ነፍሱን* ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ግን ያገኛታል።+ ማቴዎስ 16:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያገኛታል።+ ሉቃስ 9:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል።+ ዮሐንስ 12:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ* ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን* የሚጠላ+ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።+ ራእይ 12:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሱም ከበጉ ደም+ የተነሳና ከምሥክርነታቸው ቃል+ የተነሳ ድል ነሱት፤+ እስከ ሞት ድረስ እንኳ ለነፍሳቸው* አልሳሱም።+