ዘዳግም 18:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።+ ማቴዎስ 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ገና እየተናገረ ሳለም ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ ተሰማ። ሉቃስ 9:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ከዚያም ከደመናው “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ የሐዋርያት ሥራ 3:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ደግሞም ሙሴ እንዲህ ብሏል፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ* ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል።+ እሱ የሚነግራችሁንም ነገር ሁሉ ስሙ።+ 23 ያንን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።’+
22 ደግሞም ሙሴ እንዲህ ብሏል፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ* ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል።+ እሱ የሚነግራችሁንም ነገር ሁሉ ስሙ።+ 23 ያንን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።’+