ማቴዎስ 14:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ።+ በመሸም ጊዜ በዚያ ብቻውን ነበር። ማርቆስ 14:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ከዚያም ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “እኔ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።+ ሉቃስ 4:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 በነጋም ጊዜ ወጥቶ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ።+ ሕዝቡ ግን ፈልገው ፈላልገው * ያለበት ቦታ ድረስ መጡ፤ እንዳይሄድባቸውም ለመኑት። ዕብራውያን 5:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክርስቶስ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን* ከሞት ሊያድነው ለሚችለው በከፍተኛ ጩኸትና እንባ ብዙ ምልጃና ልመና አቀረበ፤+ አምላካዊ ፍርሃት ስለነበረውም ጸሎቱ ተሰማለት።
7 ክርስቶስ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን* ከሞት ሊያድነው ለሚችለው በከፍተኛ ጩኸትና እንባ ብዙ ምልጃና ልመና አቀረበ፤+ አምላካዊ ፍርሃት ስለነበረውም ጸሎቱ ተሰማለት።