ማቴዎስ 24:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “በዚያን ጊዜ ማንም ‘እነሆ፣ ክርስቶስ ይኸውላችሁ’+ ወይም ‘ያውላችሁ’ ቢላችሁ አትመኑ።+ 24 ምክንያቱም ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤+ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ።+ ሉቃስ 17:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሰዎችም ‘እዚያ ነው!’ ወይም ‘እዚህ ነው!’ ይሏችኋል። ነገር ግን አትሂዱ ወይም አትከተሏቸው።+ ሉቃስ 21:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እሱም እንዲህ አለ፦ “እንዳያሳስቷችሁ ተጠንቀቁ፤+ ብዙዎች ‘እኔ እሱ ነኝ’ እንዲሁም ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና። እነሱን አትከተሉ።+ 1 ዮሐንስ 4:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ በመንፈስ የተነገረን ቃል* ሁሉ አትመኑ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ የተነገሩት ቃላት* ከአምላክ የመነጩ መሆን አለመሆናቸውን መርምሩ፤+ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+
23 “በዚያን ጊዜ ማንም ‘እነሆ፣ ክርስቶስ ይኸውላችሁ’+ ወይም ‘ያውላችሁ’ ቢላችሁ አትመኑ።+ 24 ምክንያቱም ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤+ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ።+
4 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ በመንፈስ የተነገረን ቃል* ሁሉ አትመኑ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ የተነገሩት ቃላት* ከአምላክ የመነጩ መሆን አለመሆናቸውን መርምሩ፤+ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+