ኢሳይያስ 6:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ደጋግማችሁ ትሰማላችሁ፣ነገር ግን አታስተውሉም፤ደጋግማችሁ ታያላችሁ፣ነገር ግን ምንም እውቀት አታገኙም።’+ 10 በዓይናቸው እንዳያዩ፣በጆሯቸውም እንዳይሰሙ፣ልባቸውም እንዳያስተውል፣ተመልሰውም እንዳይፈወሱየዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤+ጆሯቸውንም ድፈን፤+ዓይናቸውንም ሸፍን።”+ ማቴዎስ 13:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በምሳሌ የምነግራቸው ለዚህ ነው፤ ቢያዩም የሚያዩት እንዲያው በከንቱ ነውና፤ ቢሰሙም የሚሰሙት እንዲያው በከንቱ ነው፤ ትርጉሙንም አያስተውሉም።+ 14 ደግሞም የኢሳይያስ ትንቢት በእነሱ ላይ እየተፈጸመ ነው። ትንቢቱ እንዲህ ይላል፦ ‘መስማቱን ትሰማላችሁ ግን በፍጹም ትርጉሙን አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ ግን በፍጹም ልብ አትሉም።+ ዮሐንስ 12:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 “በዓይናቸው አይተውና በልባቸው አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው ዓይናቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል።”+ የሐዋርያት ሥራ 28:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ‘ወደዚህ ሕዝብ ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ “መስማቱን ትሰማላችሁ፤ ግን በፍጹም አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ፤ ግን በፍጹም ልብ አትሉም።+
9 እሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ደጋግማችሁ ትሰማላችሁ፣ነገር ግን አታስተውሉም፤ደጋግማችሁ ታያላችሁ፣ነገር ግን ምንም እውቀት አታገኙም።’+ 10 በዓይናቸው እንዳያዩ፣በጆሯቸውም እንዳይሰሙ፣ልባቸውም እንዳያስተውል፣ተመልሰውም እንዳይፈወሱየዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤+ጆሯቸውንም ድፈን፤+ዓይናቸውንም ሸፍን።”+
13 በምሳሌ የምነግራቸው ለዚህ ነው፤ ቢያዩም የሚያዩት እንዲያው በከንቱ ነውና፤ ቢሰሙም የሚሰሙት እንዲያው በከንቱ ነው፤ ትርጉሙንም አያስተውሉም።+ 14 ደግሞም የኢሳይያስ ትንቢት በእነሱ ላይ እየተፈጸመ ነው። ትንቢቱ እንዲህ ይላል፦ ‘መስማቱን ትሰማላችሁ ግን በፍጹም ትርጉሙን አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ ግን በፍጹም ልብ አትሉም።+