ዘሌዋውያን 25:35, 36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 “‘በአቅራቢያህ ያለ ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ማስተዳደር ቢያቅተው አብሮህ በሕይወት ይኖር ዘንድ አንድን የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ+ እንደምትረዳ ሁሉ ልትረዳው ይገባል።+ 36 ከእሱ ወለድ ወይም ትርፍ* አትቀበል።+ ከዚህ ይልቅ አምላክህን ፍራ፤+ ወንድምህም አብሮህ በሕይወት ይኖራል። ዘዳግም 15:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* ማቴዎስ 5:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 ለሚለምንህ ስጥ፤ ሊበደርህ የሚፈልገውንም ሰው* ፊት አትንሳው።+
35 “‘በአቅራቢያህ ያለ ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ማስተዳደር ቢያቅተው አብሮህ በሕይወት ይኖር ዘንድ አንድን የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ+ እንደምትረዳ ሁሉ ልትረዳው ይገባል።+ 36 ከእሱ ወለድ ወይም ትርፍ* አትቀበል።+ ከዚህ ይልቅ አምላክህን ፍራ፤+ ወንድምህም አብሮህ በሕይወት ይኖራል።
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።*