ዘዳግም 15:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ መዝሙር 41:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል። መዝሙር 112:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በልግስና የሚያበድር ሰው ይሳካለታል።+ י [ዮድ] ጉዳዩን በፍትሕ ያከናውናል። ምሳሌ 3:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም ካለህ*+ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል።+ ምሳሌ 19:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ ማርቆስ 14:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ በፈለጋችሁ ጊዜ ሁሉ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።+ የሐዋርያት ሥራ 11:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው አቅማቸው በፈቀደ መጠን+ አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ፤+ 1 ጢሞቴዎስ 6:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+ 1 ዮሐንስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ቁሳዊ ንብረት ያለው ሰው ወንድሙ ሲቸገር ተመልክቶ ሳይራራለት ቢቀር ‘የአምላክ ፍቅር በእሱ ውስጥ አለ’ እንዴት ሊባል ይችላል?+
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+