ዘዳግም 18:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።+ ዮሐንስ 4:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ሴትየዋም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደሆንክ አሁን ተረዳሁ።+ ዮሐንስ 6:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሰዎቹም ኢየሱስ የፈጸመውን ተአምራዊ ምልክት ባዩ ጊዜ “ወደ ዓለም እንደሚመጣ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ።+ ዮሐንስ 7:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢዩ ነው” ይሉ ጀመር።+