የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 9:23-26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 ኢየሱስ ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት ሲደርስ ዋሽንት ነፊዎቹን እንዲሁም የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ+ 24 “እስቲ አንዴ ውጡ፤ ልጅቷ ተኝታለች+ እንጂ አልሞተችም” አለ። በዚህ ጊዜ በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። 25 ሕዝቡ ከወጣ በኋላ ወደ ውስጥ ገብቶ እጇን ያዛት፤+ ልጅቷም ተነሳች።+ 26 ይህም ነገር በዚያ አገር ሁሉ በሰፊው ተወራ።

  • ማርቆስ 5:38-43
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 38 ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት በደረሱም ጊዜ ትርምሱን እንዲሁም የሚያለቅሱትንና ዋይ ዋይ የሚሉትን ሰዎች ተመለከተ።+ 39 ወደ ውስጥ ከገባም በኋላ “የምታለቅሱትና የምትንጫጩት ለምንድን ነው? ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።+ 40 በዚህ ጊዜ በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። እሱ ግን ሁሉንም ወደ ውጭ ካስወጣ በኋላ የልጅቷን አባትና እናት እንዲሁም ከእሱ ጋር የነበሩትን አስከትሎ ልጅቷ ወዳለችበት ገባ። 41 ከዚያም የልጅቷን እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” ማለት ነው።+ 42 ልጅቷም ወዲያው ተነስታ መራመድ ጀመረች። (ዕድሜዋ 12 ዓመት ነበር።) ወዲያውም እጅግ ከመደሰታቸው የተነሳ የሚሆኑት ጠፋቸው። 43 እሱ ግን ይህን ለማንም እንዳይናገሩ ደጋግሞ አስጠነቀቃቸው፤*+ ለልጅቷም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት ነገራቸው።

  • ዮሐንስ 11:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይህን ከነገራቸው በኋላም “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤+ እኔም ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ” አላቸው።

  • የሐዋርያት ሥራ 7:60
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 60 ከዚያም ተንበርክኮ በታላቅ ድምፅ “ይሖዋ* ሆይ፣ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ ጮኸ።+ ይህን ከተናገረም በኋላ በሞት አንቀላፋ።

  • የሐዋርያት ሥራ 13:36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 በአንድ በኩል፣ ዳዊት በሕይወት ዘመኑ አምላክን ካገለገለ* በኋላ በሞት አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ መበስበስን አይቷል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ