የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 16:13-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ኢየሱስ ወደ ቂሳርያ ፊልጵስዩስ አካባቢ በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች፣ የሰውን ልጅ ማን ነው ይሉታል?” ሲል ጠየቃቸው።+ 14 እነሱም “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣+ ሌሎች ኤልያስ፣+ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” አሉት። 15 እሱም “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” አላቸው። 16 ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ፣+ የሕያው አምላክ ልጅ ነህ”+ ብሎ መለሰለት።

  • ማርቆስ 8:27-30
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቂሳርያ ፊልጵስዩስ መንደሮች አመሩ፤ በመንገድም ላይ ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው።+ 28 እነሱም “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣+ ሌሎች ኤልያስ፣+ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል” አሉት። 29 ከዚያም እነሱን “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ”+ ብሎ መለሰለት። 30 በዚህ ጊዜ ስለ እሱ ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አዘዛቸው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ