ኢሳይያስ 55:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+ ማቴዎስ 6:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የበደሉንን* ይቅር እንዳልን በደላችንን* ይቅር በለን።+ ማቴዎስ 18:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያም ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ይቅር ልበለው?” አለው። 22 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እስከ 77 ጊዜ* እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም።+ ቆላስይስ 3:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው+ እንኳ እርስ በርስ መቻቻላችሁንና በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።+ ይሖዋ* በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።+ 1 ጴጥሮስ 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከሁሉም በላይ አንዳችሁ ለሌላው የጠለቀ ፍቅር ይኑራችሁ፤+ ምክንያቱም ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል።+
21 ከዚያም ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ይቅር ልበለው?” አለው። 22 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እስከ 77 ጊዜ* እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም።+
13 አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው+ እንኳ እርስ በርስ መቻቻላችሁንና በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።+ ይሖዋ* በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።+