መዝሙር 41:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሌላው ቀርቶ ከእኔ ጋር ሰላም የነበረው፣ እምነት የጣልኩበትና+ከማዕዴ ይበላ የነበረ ሰው ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ።*+ ማቴዎስ 26:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እየበሉ ሳሉም “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ ማርቆስ 14:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በማዕድ ተቀምጠው እየበሉ ሳለም ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ፣ ከእኔ ጋር እየበላ ያለ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ ዮሐንስ 13:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ መንፈሱ ተረብሾ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል”+ ሲል በግልጽ ተናገረ።