ማቴዎስ 26:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እየበሉ ሳሉም “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ ማርቆስ 14:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በማዕድ ተቀምጠው እየበሉ ሳለም ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ፣ ከእኔ ጋር እየበላ ያለ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ ሉቃስ 22:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ ከእኔ ጋር በማዕድ ነው።+ ዮሐንስ 6:70 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 70 ኢየሱስም መልሶ “አሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኳችሁ እኔ አይደለሁም?+ ይሁንና ከመካከላችሁ አንዱ ስም አጥፊ* ነው” አላቸው።+