መዝሙር 110:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 110 ይሖዋ ጌታዬን “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ+በቀኜ ተቀመጥ”+ አለው። ማቴዎስ 26:64 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 64 ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው። ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ከዚህ በኋላ የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለው። ማርቆስ 14:62 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 62 ኢየሱስም “አዎ ነኝ፤ እናንተም የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለ። የሐዋርያት ሥራ 2:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ይህን ኢየሱስን አምላክ ከሞት አስነሳው፤ እኛ ሁላችንም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+ 33 ስለዚህ ወደ አምላክ ቀኝ ከፍ ከፍ ስለተደረገና+ ቃል የተገባውን ቅዱስ መንፈስ ከአብ ስለተቀበለ+ ይህን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው። የሐዋርያት ሥራ 7:55 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 እሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ወደ ሰማይ ሲመለከት የአምላክን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ ቆሞ አየ፤+ ሮም 8:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 እነሱን የሚኮንን ማን ነው? ምክንያቱም የሞተው ብሎም ከሞት የተነሳውና በአምላክ ቀኝ የተቀመጠው+ እንዲሁም ስለ እኛ የሚማልደው+ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ቆላስይስ 3:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይሁን እንጂ ከክርስቶስ ጋር አብራችሁ ከተነሳችሁ+ ክርስቶስ በአምላክ ቀኝ+ በተቀመጠበት በላይ ያሉትን ነገሮች ፈልጉ። ዕብራውያን 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እሱ የአምላክ ክብር+ ነጸብራቅና የማንነቱ ትክክለኛ አምሳያ ነው፤+ እሱም በኃያል ቃሉ ሁሉንም ነገር ደግፎ ያኖራል። እኛን ከኃጢአታችን ካነጻ+ በኋላም በሰማይ በግርማዊው ቀኝ ተቀምጧል።+
32 ይህን ኢየሱስን አምላክ ከሞት አስነሳው፤ እኛ ሁላችንም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+ 33 ስለዚህ ወደ አምላክ ቀኝ ከፍ ከፍ ስለተደረገና+ ቃል የተገባውን ቅዱስ መንፈስ ከአብ ስለተቀበለ+ ይህን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።
3 እሱ የአምላክ ክብር+ ነጸብራቅና የማንነቱ ትክክለኛ አምሳያ ነው፤+ እሱም በኃያል ቃሉ ሁሉንም ነገር ደግፎ ያኖራል። እኛን ከኃጢአታችን ካነጻ+ በኋላም በሰማይ በግርማዊው ቀኝ ተቀምጧል።+