5 ወደ መቃብሩ ሲገቡ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ። 6 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “አትደንግጡ።+ በእንጨት ላይ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እየፈለጋችሁ እንደሆነ አውቃለሁ። እሱ ተነስቷል።+ እዚህ የለም። ተመልከቱ፣ እሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውና።+ 7 ይልቁንስ ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ ‘ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል።+ እንደነገራችሁም እዚያ ታዩታላችሁ’ በሏቸው።”+