-
ማቴዎስ 14:14-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ኢየሱስ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲመጣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተመለከተና በጣም አዘነላቸው፤+ በመካከላቸው የነበሩትንም ሕመምተኞች ፈወሰ።+ 15 በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው “ቦታው ገለል ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል፤ ስለዚህ ሕዝቡ ወደ መንደሮቹ ሄደው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው” አሉት።+ 16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። 17 እነሱም “ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ በስተቀር እዚህ ምንም ነገር የለንም” አሉት።
-
-
ማርቆስ 6:35-38አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
35 ሰዓቱ እየገፋ በመሄዱ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ቦታ ራቅ ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል።+ 36 በአካባቢው ወዳሉት ገጠሮችና መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው።”+ 37 እሱም መልሶ “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። እነሱም “ሄደን በ200 ዲናር* ዳቦ ገዝተን እንዲበሉ እንስጣቸው?” አሉት።+ 38 እሱም “ስንት ዳቦ አላችሁ? እስቲ ሄዳችሁ እዩ!” አላቸው። ሄደው ካዩ በኋላ “አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ” አሉት።+
-