-
ማርቆስ 6:39-44አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
39 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በቡድን በቡድን ሆኖ በለመለመው መስክ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ።+ 40 በመሆኑም ሕዝቡ መቶ መቶና ሃምሳ ሃምሳ እየሆነ በቡድን ተቀመጠ። 41 እሱም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ።+ ከዚያም ዳቦውን ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ሁለቱን ዓሣም ለሁሉም አከፋፈለ። 42 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ 43 ከዚያም ቁርስራሹን ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ዓሣውን ሳይጨምር 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ 44 ዳቦውን የበሉትም 5,000 ወንዶች ነበሩ።
-