የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 4:42-44
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 42 ከበዓልሻሊሻ+ የመጣ አንድ ሰው ነበር፤ እሱም ለእውነተኛው አምላክ ሰው ከፍሬው በኩራት የተዘጋጁ 20 የገብስ ዳቦዎችና+ አንድ ከረጢት የእሸት ዛላዎች ይዞለት መጣ።+ ከዚያም ኤልሳዕ “ሰዎቹ እንዲበሉ ስጣቸው” አለው። 43 ሆኖም አገልጋዩ “ይህን እንዴት አድርጌ ለ100 ሰው አቀርባለሁ”+ አለው። በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ “ሰዎቹ እንዲበሉ ስጣቸው፤ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ይበላሉ፤ ደግሞም ይተርፋቸዋል’”+ አለው። 44 ከዚያም አቀረበላቸው፤ እነሱም በሉ፤ ይሖዋም በተናገረው መሠረት ተረፋቸው።+

  • ማርቆስ 6:42, 43
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 42 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ 43 ከዚያም ቁርስራሹን ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ዓሣውን ሳይጨምር 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+

  • ማርቆስ 8:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ሕዝቡም በልቶ ጠገበ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+

  • ሉቃስ 9:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+

  • ዮሐንስ 6:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በልተው ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ምንም እንዳይባክን የተረፈውን ቁርስራሽ ሁሉ ሰብስቡ” አላቸው። 13 ስለዚህ ከአምስቱ የገብስ ዳቦ ሰዎቹ በልተው የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ