የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 8:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 እነሆ፣ በጉዞ ላይ ሳሉ በባሕሩ ላይ ኃይለኛ ማዕበል ስለተነሳ ጀልባዋ በውኃ ተሞልታ ልትሰጥም ተቃረበች፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።+

  • ማቴዎስ 14:24-33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 በዚህ ጊዜ ጀልባው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሜትሮች* ከየብስ ርቆ የነበረ ሲሆን ነፋሱ ወደ እነሱ ይነፍስ ስለነበር ማዕበሉ በጣም አስቸገራቸው። 25 ሆኖም ኢየሱስ በአራተኛው ክፍለ ሌሊት* በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነሱ መጣ። 26 ደቀ መዛሙርቱ በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ደንግጠው “ምትሃት ነው!” አሉ። በፍርሃት ተውጠውም ጮኹ። 27 ሆኖም ኢየሱስ ወዲያውኑ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።+ 28 ጴጥሮስም መልሶ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ከሆንክ በውኃው ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው። 29 እሱም “ና!” አለው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ከጀልባው ላይ ወርዶ በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ። 30 ሆኖም አውሎ ነፋሱን ሲያይ ፈራ። መስጠም ሲጀምርም “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። 31 ወዲያው ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ! ለምን ተጠራጠርክ?” አለው።+ 32 ጀልባው ላይ ከወጡ በኋላ አውሎ ነፋሱ ጸጥ አለ። 33 ከዚያም በጀልባው ውስጥ ያሉት “አንተ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።*

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ