ዘዳግም 18:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።+ ዮሐንስ 6:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሰዎቹም ኢየሱስ የፈጸመውን ተአምራዊ ምልክት ባዩ ጊዜ “ወደ ዓለም እንደሚመጣ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ።+ 15 ከዚያም ኢየሱስ ሰዎቹ መጥተው ሊይዙትና ሊያነግሡት እንዳሰቡ ስላወቀ ብቻውን ዳግመኛ ወደ ተራራ ገለል አለ።+ ዮሐንስ 7:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 የበዓሉ+ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “የተጠማ ካለ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።+ ዮሐንስ 7:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢዩ ነው” ይሉ ጀመር።+ የሐዋርያት ሥራ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ደግሞም ሙሴ እንዲህ ብሏል፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ* ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል።+ እሱ የሚነግራችሁንም ነገር ሁሉ ስሙ።+
14 ሰዎቹም ኢየሱስ የፈጸመውን ተአምራዊ ምልክት ባዩ ጊዜ “ወደ ዓለም እንደሚመጣ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ።+ 15 ከዚያም ኢየሱስ ሰዎቹ መጥተው ሊይዙትና ሊያነግሡት እንዳሰቡ ስላወቀ ብቻውን ዳግመኛ ወደ ተራራ ገለል አለ።+