ማቴዎስ 7:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ፤+ 29 የሚያስተምራቸው እንደ እነሱ ጸሐፍት ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን ነበርና።+ ሉቃስ 4:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ሁሉም ስለ እሱ መልካም ነገር ይናገሩ ጀመር፤ ከአፉ በሚወጡት የሚማርኩ ቃላትም+ በመደነቅ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር።+