1 ነገሥት 1:33, 34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው፦ “የጌታችሁን አገልጋዮች ውሰዱና ልጄን ሰለሞንን በበቅሎዬ*+ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን+ ይዛችሁት ውረዱ። 34 በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡታል፤+ ከዚያም ቀንደ መለከት እየነፋችሁ ‘ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!’+ በሉ። ኢሳይያስ 62:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሆ፣ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አውጇል፦ “ለጽዮን ሴት ልጅ‘እነሆ፣ መዳንሽ ቀርቧል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ’ በሏት።”+ ዘካርያስ 9:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል።+ እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤*ትሑት ነው፤+ ደግሞም በአህያ፣በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ* ላይ ይቀመጣል።+ ማቴዎስ 21:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፦ ‘እነሆ ንጉሥሽ+ ገር+ ሆኖ በአህያ፣ አዎ በአህያይቱ ግልገል በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል።’”+
33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው፦ “የጌታችሁን አገልጋዮች ውሰዱና ልጄን ሰለሞንን በበቅሎዬ*+ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን+ ይዛችሁት ውረዱ። 34 በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡታል፤+ ከዚያም ቀንደ መለከት እየነፋችሁ ‘ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!’+ በሉ።
11 እነሆ፣ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አውጇል፦ “ለጽዮን ሴት ልጅ‘እነሆ፣ መዳንሽ ቀርቧል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ’ በሏት።”+
9 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል።+ እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤*ትሑት ነው፤+ ደግሞም በአህያ፣በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ* ላይ ይቀመጣል።+