ሮም 13:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እርስ በርስ ከመዋደድ በቀር በማንም ላይ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤+ ሰውን የሚወድ ሁሉ ሕጉን ፈጽሟልና።+ 1 ቆሮንቶስ 13:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ፍቅር ለዘላለም ይኖራል።* ሆኖም የመተንበይ፣ በልሳን የመናገርም* ሆነ የእውቀት ስጦታ ይቀራል። 1 ቆሮንቶስ 13:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሁን እንጂ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ ይቀጥላሉ፤ ከእነዚህ መካከል የሚበልጠው ግን ፍቅር ነው።+ 1 ዮሐንስ 4:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ማንም “አምላክን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን የሚጠላ ከሆነ ይህ ሰው ውሸታም ነው።+ ያየውን ወንድሙን የማይወድ+ ያላየውን አምላክ ሊወድ አይችልምና።+