ማቴዎስ 10:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ይሁን እንጂ አሳልፈው ሲሰጧችሁ እንዴት ወይም ምን ብለን እንመልሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ የምትናገሩት ነገር በዚያኑ ሰዓት ይሰጣችኋልና፤+ 20 በምትናገሩበት ጊዜ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ይልቁንም በእናንተ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው።+ ዮሐንስ 16:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሁን እንጂ እሱ* ይኸውም የእውነት መንፈስ+ ሲመጣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም የሚናገረው ከራሱ አመንጭቶ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰማውን ይናገራል፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ያሳውቃችኋል።+ 1 ቆሮንቶስ 2:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 እኛ አምላክ በደግነት የሰጠንን ነገሮች ማወቅ እንድንችል ከአምላክ የሆነውን መንፈስ+ ተቀበልን እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1 ዮሐንስ 2:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እናንተ ግን ከእሱ የተቀበላችሁት የመንፈስ ቅብዓት+ በውስጣችሁ ይኖራል፤ በመሆኑም ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ያገኛችሁት ይህ ቅብዓት ስለ ሁሉም ነገር እያስተማራችሁ ነው፤+ ደግሞም እውነት እንጂ ውሸት አይደለም። ይህ ቅብዓት ባስተማራችሁ መሠረት ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ።+
19 ይሁን እንጂ አሳልፈው ሲሰጧችሁ እንዴት ወይም ምን ብለን እንመልሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ የምትናገሩት ነገር በዚያኑ ሰዓት ይሰጣችኋልና፤+ 20 በምትናገሩበት ጊዜ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ይልቁንም በእናንተ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው።+
13 ይሁን እንጂ እሱ* ይኸውም የእውነት መንፈስ+ ሲመጣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም የሚናገረው ከራሱ አመንጭቶ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰማውን ይናገራል፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ያሳውቃችኋል።+
27 እናንተ ግን ከእሱ የተቀበላችሁት የመንፈስ ቅብዓት+ በውስጣችሁ ይኖራል፤ በመሆኑም ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ያገኛችሁት ይህ ቅብዓት ስለ ሁሉም ነገር እያስተማራችሁ ነው፤+ ደግሞም እውነት እንጂ ውሸት አይደለም። ይህ ቅብዓት ባስተማራችሁ መሠረት ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ።+