ማቴዎስ 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲነቅፏችሁ፣+ ስደት ሲያደርሱባችሁና+ ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲያስወሩባችሁ ደስተኞች ናችሁ።+ ማቴዎስ 10:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል፤+ እስከ መጨረሻው የጸና* ግን ይድናል።+ ማቴዎስ 24:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣+ ይገድሏችኋል+ እንዲሁም በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።+ 2 ጢሞቴዎስ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በእርግጥም የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመሆን ለአምላክ ያደሩ ሆነው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ስደት ይደርስባቸዋል።+ 1 ጴጥሮስ 2:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ደግሞም የተጠራችሁት በዚህ ጎዳና እንድትሄዱ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስም እንኳ የእሱን ፈለግ በጥብቅ እንድትከተሉ አርዓያ ትቶላችሁ+ ስለ እናንተ መከራ ተቀብሏል።+
21 ደግሞም የተጠራችሁት በዚህ ጎዳና እንድትሄዱ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስም እንኳ የእሱን ፈለግ በጥብቅ እንድትከተሉ አርዓያ ትቶላችሁ+ ስለ እናንተ መከራ ተቀብሏል።+