የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 26:69, 70
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 69 ጴጥሮስ ከቤት ውጭ፣ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ወደ እሱ መጥታ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።+ 70 እሱ ግን “ስለ ምን እየተናገርሽ እንዳለ አላውቅም” በማለት በሁሉም ፊት ካደ።

  • ማርቆስ 14:66-68
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 66 ጴጥሮስ ግቢው ውስጥ በታች በኩል ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ሴት አገልጋዮች አንዷ መጣች።+ 67 እሳት ሲሞቅ አይታ ትኩር ብላ ተመለከተችውና “አንተም ከዚህ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ” አለችው። 68 እሱ ግን “ሰውየውን አላውቀውም፤ ምን እንደምታወሪም አላውቅም” ሲል ካደ፤ ከዚያም ወደ መግቢያው* ሄደ።

  • ሉቃስ 22:55-57
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 55 በግቢው መካከል እሳት አንድደው አንድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ተቀመጠ።+ 56 ይሁንና አንዲት አገልጋይ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሲሞቅ አየችውና ትኩር ብላ ከተመለከተችው በኋላ “ይህ ሰውም ከእሱ ጋር ነበር” አለች። 57  እሱ ግን “አንቺ ሴት፣ እኔ አላውቀውም” ሲል ካደ።

  • ዮሐንስ 18:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ “አንተም ከእሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አሉት። እሱም “አይደለሁም” ሲል ካደ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ