የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 21:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና+ በእንጨት ላይ ብትሰቅለው+ 23 በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር።+ ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤+ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ።+

  • ማቴዎስ 27:57-60
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 57  ቀኑ በመገባደድ ላይ ሳለ የአርማትያስ ሰው የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሀብታም መጣ፤ እሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።+ 58 ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጠየቀ።+ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።+ 59 ከዚያም ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ በንጹሕ በፍታ ገነዘው፤+ 60 ከዓለት ፈልፍሎ በሠራው በራሱ አዲስ መቃብር ውስጥም አኖረው።+ ከዚያም አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋውና ሄደ።

  • ማርቆስ 15:43-46
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 43 የተከበረ የሸንጎ* አባል የሆነውና የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ መጣ። ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ።+ 44 ጲላጦስ ግን ኢየሱስ ሞቶ እንደሆነ ለማወቅ የመቶ አለቃውን ጠርቶ በእርግጥ ሞቶ እንደሆነ ጠየቀው። 45 መሞቱን ከመቶ አለቃው ካረጋገጠ በኋላም አስከሬኑን እንዲወስድ ለዮሴፍ ፈቀደለት። 46 እሱም በፍታ ገዝቶ አስከሬኑን ካወረደ በኋላ በበፍታው ገነዘው፤ ከዚያም ከዓለት ተፈልፍሎ በተሠራ መቃብር ውስጥ አኖረው፤+ ድንጋይ አንከባሎም የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ