ሮም 5:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል።+ ሮም 8:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ለገዛ ልጁ እንኳ ያልሳሳው፣ ከዚህ ይልቅ ለእኛ ለሁላችን አሳልፎ የሰጠው+ አምላክ፣ ከእሱ ጋር አብሮ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ እንዴት በደግነት አይሰጠንም? 1 ዮሐንስ 4:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የአምላክ ፍቅር ከእኛ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዚህ መንገድ ተገልጧል፤ እኛ በእሱ አማካኝነት ሕይወት ማግኘት እንድንችል+ አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታል።+ 10 ይህ ፍቅር የተገለጠው በዚህ መንገድ ነው፦ እኛ አምላክን ስለወደድነው ሳይሆን እሱ ስለወደደንና ለኃጢአታችን የማስተሰረያ መሥዋዕት* እንዲሆን+ ልጁን ስለላከ ነው።+ 1 ዮሐንስ 4:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እሱ አስቀድሞ ስለወደደን እኛም ፍቅር እናሳያለን።+
9 የአምላክ ፍቅር ከእኛ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዚህ መንገድ ተገልጧል፤ እኛ በእሱ አማካኝነት ሕይወት ማግኘት እንድንችል+ አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታል።+ 10 ይህ ፍቅር የተገለጠው በዚህ መንገድ ነው፦ እኛ አምላክን ስለወደድነው ሳይሆን እሱ ስለወደደንና ለኃጢአታችን የማስተሰረያ መሥዋዕት* እንዲሆን+ ልጁን ስለላከ ነው።+